ስለ እኛ

ስለ እኛ

የኢሚግሬሽን ጉዳዮች የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት

ኸርመን የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት ፣ ከመላው ዓለም የመጡ ስደተኞችን በማማከር እና ለመብታቸው በመሟገት በርካታ አስርተ ዓመታትን አሳልፈናል፡፡ በክሊቭላንድ ፣ ኮለምበስ ፣ ዲትሮይት ፣ ቶሌዶ ፣ ያንግስታወን ፣ ዴይተን ፣ ሲንሲናቲ ፣ ፒስበርግ እና ቡፋሎ ውስጥ የሚገኙት ሐቀኛ እና ርህሩህ የኢሚግሬሽን ጠበቆቻችን ቡድን የስደተኞችን እይታ ትክክለኛ ግንዛቤ ይሰጣሉ። ይህም የደንበኞቻችን ባሕሎች ፣ እሴቶች እና እምነቶች ሙሉ በሙሉ መገንዘብ እና ማድነቅንም ያካትታል ፡፡

የኢሚግሬሽን ጠበቆቻችን አረብኛ ስፓኒሽ ጃፓንኛ እና ሩሲያኛን ጨምሮ 12 የተለያዩ ቋንቋዎችን ይናገራሉ። ከደንበኞቻችን ጋር በግልጽ መነጋገር መቻላችን እውነታውን በትክክል በማግኘት እና በችሎት ደንበኞቹን በላቀ ሁኔታ እንድንወክ አስችሎናል።

የትም ይሁኑ የትም በአሜሪካም ሆነ በውጭ ሀገር ሁኔታዎን በጥንቃቄ እናዳምጥዎታለን እናም አማራጮችን ከእርስዎ ጋር ወዳጃዊ በሆነ መንገድ እና በቀላሉ እንነጋገራለን፡፡ እኛ ለስደተኞች እና ቤተሰቦቻቸው እንጨነቃለን እንዲሁም ለወራት መዘግየት እና በሺዎች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚያስወጣ የተለመዱ ስህተቶችን እንዲያስወግዱ ልንረዳቸው እንችላለን ፡፡

ዛሬውኑ ያግኙን

Law 6
Immigration Lawyers Ohio - Herman Legal Group

በስደተኞች ላይ መጽሐፍ

Attorney Richard Herman

ኸርመን የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት መስራች ሪቻርድ ኸርማን ለስደተኞች አለም አቀፍ ጠበቃ ነው ፡፡ ስደተኞች የአሜሪካንን ጥንካሬ እና ተስፋ እንደሚስሉ በእውነት ያምናሉ ፡፡ ስደተኛው የሠራተኛ ኃይል ለአሜሪካ  በሚያበረክተው አስተዋፆ ላይ ሪቻርድ በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆነImmigrant, Inc.: Why Immigrant Entrepreneurs Are Driving The New Economy በሚል በጋራ የፃፉት የስኬት ታሪኮች እና ምርምር  ስደተኞችን እና  አሜሪካን የሚመለከቱበትን መንገድ እስከመጨረሻው የሚቀይር አንድ ጠንካራ ድርሰት ነው፡፡

ስለ ሪቻርድ መጽሐፍ እዚህ የበለጠ ይረዱ።

ታሪካችን

ኸርመን የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት የተቋቋመው 1995 በክሊቭላንድ ኦሃዮ ተወላጅ በሆነው ሪቻርድ ኸርማን ነው ፡፡ ሪቻርድ በመጀመሪያ ዓለም አቀፍ የንግድ ህግ ላይ በጥብቅና ያገለገሉ የነበረ ሲሆን ፣ ነገር ግን ከነበራቸው ልምድ ስደተኞች በንግድ ስራዎቻቸው ብቻ ሳይሆን በግል ህይወታቸውም ለመበልፀግ እየሞከሩ ያሉበትን የላቀ የህግ ድጋፉ ፍላጎቶችን መገንዘብ ችለዋል ፡፡ ከዚያን ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ የኢሚግሬሽን ጠበቃ ሪቻርድ እና የእርሱ ቡድን ስደተኞችን በመርዳት 20 ዓመታት ያህል ልምድ አዳብረዋል ፡፡

በክሊቭላንድ አከባቢ ሪቻርድ የስደተኛውን ማህበረሰብ ለማጠንከር የረዳ ሲሆን ድጋፍ ለሚስፈልጋቸው መስጠቱን ቀጥሏል ፡፡ ሪቻርድ ክሊቭላንድ እና ሌሎች ዋና ዋና ከተሞች በእድገት ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ያምናሉ ፡፡ ኸርመን የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት በኦሃዮ እና ሚሺገን ውስጥ ባሉት ሰባት አካባቢዎች የኢሚግሬሽን የጥብቅና አገልግሎት ቢሮዎች ለመክፈት የቻልን ሲሆን በአሜሪካ እና በውጭ አገር በሙሉ ደንበኞችን ለማገልገል የሚያስችል አቅም አለን፡፡

ዕውቅና

ነገሮችን እናከናውናለን እንዲሁም በትክክል ለስደተኞች እንሰራለን፡፡ የእኛ ስኬት እና ቆራጥ ሁኔታ ሳይስተዋል አልቀረም፡፡ በብዙ ብሔራዊ ሕትመቶች ላይ   ልዩ የኢሚግሬሽን ሕግ ባለሞያዎች/Expert ሆነን ቀርበናል፡፡ ሪቻርድ ኸርመን በኢሚግሬሽን በዓለም አቀፍ ብዝሀነት እና በዓለም አቀፍ ንግድ ብሔራዊ ዝነኛ ተንታኝ ለመሆን የቻለ ሲሆን የሚከተሉትን ጨምሮ በብዙ ብሔራዊ ሚዲያዎች ቀርቧል ፡፡

The New York Times logo - Recognition
The Washington Times Logo- Recognition
San Francisco Chronicle Logo - Recognition
USA Today Logo - Recognition
Forbes Logo - Recognition
npr-recognition
Bloomberg Businessweek Logo - Recognition
The O'Reilly Factor Logo - Recognition
PC World Logo - Recognition
CIO Magazine Logo - Recognition
CW Computerworld Logo - Recognition
Information Week Logo - Recognition

የተልእኮ እና ራዕይያችን መግለጫ

ድርጅታችን  የቤተሰብ ኢሚግሬሽን ፣ የሥራ ቅጥር ኢሚግሬሽን    ዜግነት ዲፖርቴሽን ፣    የማግለልን/Exclusion  እና የኢንቨስትመንት ኢሚግሬሽን ሕግን ጨምሮ በሀገሪቱ አጠቃላይ የኢሚግሬሽን ህግ  ስፔሻላይዝ  ያደረገ በአሜሪካን ሀገር ቀደምት ብሔራዊ የጥብቅና አገልግሎት ተቋም ነው ፡፡ ቆራጥ የሆነው  የጠበቆች ቡድናችን ዜጋ ሆኑም አሆልኑም ፣ የተመዘገቡም ሆኑ  ያልተመዘገቡ  በሕገመንግስቱ እንደተረጋገጠው የስደተኞች መብቶችን እና ነጻነትን በሕግ በተደነገገው መሠረት  በከፍተኛ ደረጃ ያስጠብቃል፡፡ የሁሉም ህዝብ ብዝሃነትን እና እኩልነትን እናበረታታለን እንዲሁም ስደተኞች አሜሪካን ጠንካራ ያደርጓታል በሚል እምነት ለስደተኞች መብቶች ተሟጋቾች ለመሆን እንጥራለን ፡፡

metal justice statue

ለማኅበረሰባችን የምናደርገው መልካም አስተዋፆ

የብዝሃነታችን እና የእኩልነት ተልእኳችን ጋር ተያያዥነት ላላቸው ሲቪካዊ ምክንያቶች በየዓመቱ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰአታት ሕዝባዊ አገልግሎቶችን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ዶላሮችን እንለግሳለን ፡፡ ማህበራዊ ኃላፊነት የራሳችንን ባህል እና አስተሳሰብን ይመራል ፡፡

ከኸርመን የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት ጋር በመጠኑ ስለተዋወቁ እናመሰግናለን። ማንኛውንም ጥያቄ ካሎት እባክዎን በስልክ ቁጥር +1 (216) 696-6170 ይደውሉልን ፡፡

ለኸርማን ህጋዊ ቡድን የወደፊት ዕጣህ ቅድሚያ ነው።
አሁን ይደውሉልን እና ምክክር ያግኙ
24/7 ምሽቶች እና ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ