ስለ እኛ

የእርስዎ ማራኪ ርዕስ የታመነ እና ልምድ ያለው የኢሚግሬሽን ጠበቆች በኦክላሆማ፣ አካባቢው እና በመላው ዩናይትድ ስቴትስ።

ስለ Herman Legal Group, LLC

ኸርመን የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት ፣ ከመላው ዓለም የመጡ ስደተኞችን በማማከር እና ለመብታቸው በመሟገት በርካታ አስርተ ዓመታትን አሳልፈናል፡፡ በክሊቭላንድ ፣ ኮለምበስ ፣ ዲትሮይት ፣ ቶሌዶ ፣ ያንግስታወን ፣ ዴይተን ፣ ሲንሲናቲ ፣ ፒስበርግ እና ቡፋሎ ውስጥ የሚገኙት ሐቀኛ እና ርህሩህ የኢሚግሬሽን ጠበቆቻችን ቡድን የስደተኞችን እይታ ትክክለኛ ግንዛቤ ይሰጣሉ። ይህም የደንበኞቻችን ባሕሎች ፣ እሴቶች እና እምነቶች ሙሉ በሙሉ መገንዘብ እና ማድነቅንም ያካትታል ፡፡

የኢሚግሬሽን ጠበቆቻችን አረብኛ ፣ ስፓኒሽ ፣ ጃፓንኛ እና ሩሲያኛን ጨምሮ 12 የተለያዩ ቋንቋዎችን ይናገራሉ። ከደንበኞቻችን ጋር በግልጽ መነጋገር መቻላችን እውነታውን በትክክል በማግኘት እና በችሎት ደንበኞቹን በላቀ ሁኔታ እንድንወክ አስችሎናል።

የትም ይሁኑ የትም በአሜሪካም ሆነ በውጭ ሀገር ሁኔታዎን በጥንቃቄ እናዳምጥዎታለን እናም አማራጮችን ከእርስዎ ጋር ወዳጃዊ በሆነ መንገድ እና በቀላሉ እንነጋገራለን፡፡ እኛ ለስደተኞች እና ቤተሰቦቻቸው እንጨነቃለን እንዲሁም ለወራት መዘግየት እና በሺዎች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚያስወጣ የተለመዱ ስህተቶችን እንዲያስወግዱ ልንረዳቸው እንችላለን ፡፡

Immigration Lawyers Ohio - Herman Legal Group

በስደተኞች ላይ መጽሐፍ

ኸርመን የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት መስራች ሪቻርድ ኸርማን ለስደተኞች አለም አቀፍ ጠበቃ ነው ፡፡ ስደተኞች የአሜሪካንን ጥንካሬ እና ተስፋ እንደሚስሉ በእውነት ያምናሉ ፡፡ ስደተኛው የሠራተኛ ኃይል ለአሜሪካ  በሚያበረክተው አስተዋፆ ላይ ሪቻርድ በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆነ “Immigrant, Inc.: Why Immigrant Entrepreneurs Are Driving The New Economy” ፣ በሚል በጋራ የፃፉት የስኬት ታሪኮች እና ምርምር  ስደተኞችን እና  አሜሪካን የሚመለከቱበትን መንገድ እስከመጨረሻው የሚቀይር አንድ ጠንካራ ድርሰት ነው፡፡

ስለ ሪቻርድ መጽሐፍ እዚህ የበለጠ ይረዱ።

ታሪካችን

ኸርመን የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት የተቋቋመው በ 1995 በክሊቭላንድ ኦሃዮ ተወላጅ በሆነው ሪቻርድ ኸርማን ነው ፡፡ ሪቻርድ በመጀመሪያ ዓለም አቀፍ የንግድ ህግ ላይ በጥብቅና ያገለገሉ የነበረ ሲሆን ፣ ነገር ግን ከነበራቸው ልምድ ስደተኞች በንግድ ስራዎቻቸው ብቻ ሳይሆን በግል ህይወታቸውም ለመበልፀግ እየሞከሩ ያሉበትን የላቀ የህግ ድጋፉ ፍላጎቶችን መገንዘብ ችለዋል ፡፡ ከዚያን ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ የኢሚግሬሽን ጠበቃ ሪቻርድ እና የእርሱ ቡድን ስደተኞችን በመርዳት የ 20 ዓመታት ያህል ልምድ አዳብረዋል ፡፡

በክሊቭላንድ አከባቢ ሪቻርድ የስደተኛውን ማህበረሰብ ለማጠንከር የረዳ ሲሆን ድጋፍ ለሚስፈልጋቸው መስጠቱን ቀጥሏል ፡፡ ሪቻርድ ክሊቭላንድ እና ሌሎች ዋና ዋና ከተሞች በእድገት ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ያምናሉ ፡፡ ኸርመን የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት በኦሃዮ እና ሚሺገን ውስጥ ባሉት ሰባት አካባቢዎች የኢሚግሬሽን የጥብቅና አገልግሎት ቢሮዎች ለመክፈት የቻልን ሲሆን በአሜሪካ እና በውጭ አገር በሙሉ ደንበኞችን ለማገልገል የሚያስችል አቅም አለን፡፡

የተልእኮ እና ራዕይያችን መግለጫ

ድርጅታችን  የቤተሰብ ኢሚግሬሽን ፣ የሥራ ቅጥር ኢሚግሬሽን  ፣  ዜግነት ፣ ዲፖርቴሽን ፣    የማግለልን/Exclusion  እና የኢንቨስትመንት ኢሚግሬሽን ሕግን ጨምሮ በሀገሪቱ አጠቃላይ የኢሚግሬሽን ህግ  ስፔሻላይዝ  ያደረገ በአሜሪካን ሀገር ቀደምት ብሔራዊ የጥብቅና አገልግሎት ተቋም ነው ፡፡ ቆራጥ የሆነው  የጠበቆች ቡድናችን ዜጋ ሆኑም አሆልኑም ፣ የተመዘገቡም ሆኑ  ያልተመዘገቡ  ፣ በሕገ–መንግስቱ እንደተረጋገጠው የስደተኞች መብቶችን እና ነጻነትን በሕግ በተደነገገው መሠረት  በከፍተኛ ደረጃ ያስጠብቃል፡፡ የሁሉም ህዝብ ብዝሃነትን እና እኩልነትን እናበረታታለን እንዲሁም ስደተኞች አሜሪካን ጠንካራ ያደርጓታል በሚል እምነት ለስደተኞች መብቶች ተሟጋቾች ለመሆን እንጥራለን ፡፡

ለማኅበረሰባችን የምናደርገው መልካም አስተዋፆ

የብዝሃነታችን እና የእኩልነት ተልእኳችን ጋር ተያያዥነት ላላቸው ሲቪካዊ ምክንያቶች በየዓመቱ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰአታት ሕዝባዊ አገልግሎቶችን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ዶላሮችን እንለግሳለን ፡፡ ማህበራዊ ኃላፊነት የራሳችንን ባህል እና አስተሳሰብን ይመራል ፡፡

ከኸርመን የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት ጋር በመጠኑ ስለተዋወቁ እናመሰግናለን። ማንኛውንም ጥያቄ ካሎት እባክዎን በስልክ ቁጥር +1 (216) 696-6170 ይደውሉልን ፡፡

ዕውቅና

ነገሮችን እናከናውናለን ፣ እንዲሁም በትክክል ለስደተኞች እንሰራለን፡፡ የእኛ ስኬት እና ቆራጥ ሁኔታ ሳይስተዋል አልቀረም፡፡ በብዙ ብሔራዊ ሕትመቶች ላይ   ልዩ የኢሚግሬሽን ሕግ ባለሞያዎች/Expert ሆነን ቀርበናል፡፡ ሪቻርድ ኸርመን በኢሚግሬሽን ፣ በዓለም አቀፍ ብዝሀነት እና በዓለም አቀፍ ንግድ ብሔራዊ ዝነኛ ተንታኝ ለመሆን የቻለ ሲሆን የሚከተሉትን ጨምሮ በብዙ ብሔራዊ ሚዲያዎች ቀርቧል ፡፡

የባለሙያ የህግ እገዛ በ Herman Legal Group, LLC

24/7 ድጋፍ ፣ ራቅ ጥሪ ብቻ!